(ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም) የሪፎርም ቀን፣ የአዲስ ዓመት ዋዜማና የክቡር አምባሳደርን ትውውቅ ምክንያት በማድረግ በሞስኮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችና የሚሲዮኑ ሰራተኞች በጋራ በመሆን በኤምባሲው አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ክቡር አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) ራሳቸውን በማስተዋወቅ በዓሉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከሪፎርሙ በኋላ በአገር ዓቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግባራትን ዝርዝር ማብራሪያ በማቅረብ ያስረዱ ሲሆን ስራቸው ተጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የተደረጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ በመንከባከብ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባን እንዲሁም በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ አገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን ከፍጻሜ ለማድረስ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ዳያስፖራውና ተማሪዎችም በተወካዮቻቸው አማካይነት ለክቡር አምባሳደሩ የእንኳን ደህና መጡና የእለቱን በዓላት በማስመልከት መልእክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።

ክቡር አምባሳደር ከታዳሚው ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ለዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ከዳያስፓራውና ከተማሪ ተወካዮች ጋር በመሆን ቆርሰዋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብና የቡና እንዲሁም የሙዚቃ መስተንግዶ ተካሂዶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook