Vital Events

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ (የልደት፣ጋብቻ፣ፍቺ እና ሞት) የምስክር ወረቀት

የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣መስፈርቶች እና ደጋፊ ማስረጃዎች፣
የልደት ምዝገባ
  • የልደት ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈርቶች፡-
  • አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ ወይም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  • በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  • የልደት አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት የተከሰተን ልደት ምዝገባን አይጨምርም፡፡
  • የህጻኑ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሕጋዊ የአሳዳሪነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ዕድሜው አስራ ስምንት ዓመትና በላይ የሆነ ስደተኛ ወላጆቹን የሚገልፅ ማስረጃ ከስደተኞች መረጃ ዳታ ቤዝ ላይ መረጃው የሌለ እንደሆነ ስደተኛውን በመጠየቅ መመዝገብ አለበት፡፡
  • የልደት ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 30 ዶላር ብቻ ነው።
የጋብቻ ምዝገባ

የጋብቻ ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈርቶች፡-

  • ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለኢምባሲው ማስታወቅ አለባቸው፡፡ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም፡፡
  • የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግስቱ ጋብቻው የሚፈፀምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡
  • ተጋቢዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም የስደተኝነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትን ሊገልፅ የሚችል ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ከ6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ጉርድ ፎቶግራፍ መቅረብ አለበት፡፡
  • በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡
  • የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡
  • በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክርነት ወረቀት ማቅረብ አለባት/በት።
  • ሙሽራዋ/ው ከዚህ በፊት አግብታ/ቶ የሞተባት/ችበት ከሆነ የሞት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባት/በት።
  • ተጋቢው ስደተኛ ከሆነ የስደተኝነት እውቅና ያገኘ መሆን አለበት፡፡
  • ማንኛውም ጋብቻ በኢትዮጵያ/ በፌዴራል የቤተሰብ ህግ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
  • በማንኛውም ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት፡፡
  • የጋብቻ ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 30 ዶላር ብቻ ነው።
የፍቺ ምዝገባ

የፍቺ ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ቅድመ  ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች፡-

  • ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሆን አለበት፣
  • የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት፡፡
  • ተፋቺው ስደተኛ ከሆነ የስደተኝነት እውቅና ያገኘ መሆን አለበት፡፡
  • ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ስደተኝነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ ከሆነ መመለስ አለበት፡፡
  • የፍቺ ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 30 ዶላር ብቻ ነው።
የሞት ምዝገባ

የሞት ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፣

  • ሞቱን ለማስመዝገብ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
  • የሟች ማንነት የሚገልጽ ማሰረጃ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ሊሴ-ፓሴ ወይም ማህበራዊ መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡
  • የሞት አስመዝጋቢ ከሀገሩ መንግሥት የሞት ምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሞቱን የሚያስመዘግበው ፖሊስ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ/ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
  • የሞት ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 20 ዶላር ብቻ ነው።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook